የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16-21

ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16-21 አማ2000

እርስ በር​ሳ​ች​ሁም በአ​ንድ ዐሳብ ተስ​ማሙ፤ ትዕ​ቢ​ትን ግን አታ​ስቡ፤ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ው​ንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋ​ቆች ነን አት​በሉ። ክፉ ላደ​ረ​ገ​ባ​ች​ሁም ክፉ አት​መ​ል​ሱ​ለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ​ውን ተነ​ጋ​ገሩ። ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰ​ላም ኑሩ። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ራሳ​ችሁ አት​በ​ቀሉ፤ ቍጣን አሳ​ል​ፏት፥ “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔ ብድ​ራ​ትን እከ​ፍ​ላ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና። ጠላ​ትህ ቢራብ አብ​ላው፤ ቢጠ​ማም አጠ​ጣው፤ ይህን ብታ​ደ​ርግ የእ​ሳት ፍሕም በራሱ ላይ ትከ​ም​ራ​ለህ። ክፉ​ውን በመ​ል​ካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉ​ውን በክፉ ድል አት​ን​ሣው።