ወደ ሮሜ ሰዎች 11:7-12

ወደ ሮሜ ሰዎች 11:7-12 አማ2000

እን​ግ​ዲህ ምን​ድን ነው? እስ​ራ​ኤል የፈ​ለ​ገ​ውን አላ​ገ​ኘም። የተ​መ​ረ​ጠው ግን አግ​ኝ​ቶ​አል፤ የቀ​ሩ​ትም ታወሩ። መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደን​ዛዛ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።” ዳዊ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ወጥ​መ​ድና አሽ​ክላ፥ መሰ​ና​ከ​ያና ፍዳም ትሁ​ን​ባ​ቸው። እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ይጨ​ልሙ፤ ዘወ​ት​ርም ጀር​ባ​ቸው ይጕ​በጥ።” እን​ግ​ዲህ እላ​ለሁ፤ ሊወ​ድቁ ተሰ​ና​ከ​ሉን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል ይቀኑ ዘንድ እነ​ርሱ በመ​ሰ​ና​ከ​ላ​ቸው ለአ​ሕ​ዛብ ድኅ​ነት ሆነ። የእ​ነ​ርሱ መሰ​ና​ከል ለዓ​ለም ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በደ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ባለ​ጸ​ግ​ነት ከሆነ ፍጹ​ም​ነ​ታ​ቸ​ውማ እን​ዴት በሆነ ነበር?