መዝሙረ ዳዊት 97
97
የዳዊት መዝሙር።
1ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፥
የእግዚአብሔር ሥራ፥
የቀኙ ማዳን፥ የተቀደሰ ክንዱም ድንቅ ነውና።
2እግዚአብሔር ማዳኑን አሳየ።#ዕብ. “አስታወቀ” ይላል።
በአሕዛብም ፊት ቃል ኪዳኑን ገለጠ።
3ለያዕቆብ ይቅርታውን ለእስራኤልም ቤት እውነቱን አሰበ፤
የምድር ዳርቻዎች ሁሉ፥ የአምላካችንን ማዳን እዩ።
4በምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤
አመስግኑ፥ ደስም ይበላችሁ፥ ዘምሩም።
5ለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥
በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።
6በነጋሪትና በመለከት ድምፅ፥
በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።
7ባሕር በሞላዋ፥
ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ይናወጡ።
8ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥
ተራሮች ደስ ይበላቸው፥
9ለምድር በዚያ ይፈረድላታልና።
ለዓለምም በእውነት ይፈረድላታልና።
ለአሕዛብም በቅንነት ይፈረዳል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 97: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ