መዝ​ሙረ ዳዊት 87:5-7

መዝ​ሙረ ዳዊት 87:5-7 አማ2000

እንደ ተገ​ደ​ሉና በመ​ቃ​ብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ደ​ማ​ታ​ስ​ባ​ቸው በሙ​ታን መካ​ከል የተ​ጣ​ልሁ ሆንሁ፤ እነ​ርሱ ከእ​ጅህ ርቀ​ዋ​ልና። በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታ​ች​ኛው ጕድ​ጓድ አስ​ቀ​መ​ጡኝ። በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ሁሉ በእኔ ላይ አመ​ጣህ።