መዝሙረ ዳዊት 65
65
ለመዘምራን አለቃ የመነሣት የምስጋና መዝሙር።
1በምድር ያላቸሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥
2ለስሙም ዘምሩ፥ ለክብሩም ምስጋናን ስጡ።
3እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፥ “ሥራህ ግሩም ነው፤
ኀይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶችህ ዋሹብህ።”
4ምድር ሁላ ለአንተ ትሰግዳለች፥
ለአንተም ትገዛለች፥
ለስምህም ትዘምራለች።
5የእግዚአብሔርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ።
ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።
6ባሕርን የብስ አደረጋት፥
ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፤
በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።
7በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤
ዐይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፤
የምታውቁ#ዕብ. “ዐመፀኞች” ይላል። ራሳችሁን ከፍ ከፍ አታድርጉ።
8አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን አመስግኑ፥
የምስጋናውንም ቃል አድምጡ።
9ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥
ለእግሮቼም ሁከትን አልሰጠም።
10አቤቱ፥ ፈትነኸናልና፥
ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና።
11ወደ ወጥመድም አገባኸን፥
በፊታችንም መከራን አመጣህ።
12በራሳችን ላይ ሰውን አስጫንህ፤
በእሳትና በውኃ መካከል አሳለፍኸን፥
ወደ ዕረፍትም አወጣኸን።
13መባዬን ይዤ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሚቃጠል መሥዋዕት” ይላል። ወደ ቤትህ እገባለሁ፤
14በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን
በከንፈሮቼም ያልሁትን ስእለቴን
ለአንተ እሰጣለሁ።
15ከዕጣንና ከሙክቶች ጋር
ነውር የሌለበት ንጹሕ መሥዋዕትን አቀርብልሃለሁ፤
ላሞችንና ፍየሎችንም እሠዋልሃለሁ።
16እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፤
ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።
17በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፥
በአንደበቴም ከፍ ከፍ አደረግሁት።#ግእዝ “ጮኽኹ” ይላል።
18በልቤስ በደልን አይቶ ቢሆን
እግዚአብሔር አይሰማኝም ነበር።
19ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፤
የልመናዬንም ድምፅ አደመጠ።
20ጸሎቴን ያልከለከለኝ፥
ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ፥
እግዚአብሔር ይመስገን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 65: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ