መዝሙረ ዳዊት 60
60
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
1አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬን ስማኝ፥
ጸሎቴንም አድምጠኝ።
2ልቤ ተስፋ በቈረጠ ጊዜ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
በድንጋይ ላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ።
3በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤
ተስፋዬም ሆነኽልኛልና መራኸኝ።
4በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፤
በክንፎችህ ጥላም እጋረዳለሁ፤
5አምላኬ፥ አንተ ጸሎቴን#ዕብ. “ስእለቴን” ይላል። ሰምተሃልና፤
ለሚፈሩህም ርስትን ሰጠሃቸው።
6ለንጉሥ ከቀን በላይ ቀንን ትጨምራለህ፥#በግእዝ 3ኛ መደብ።
ዓመታቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናሉ።
7በእግዚአብሔርም ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፤
ይቅርታውንና ጽድቁን ማን ይፈልጋል?
8እንዲሁ ለስምህ ለዘለዓለም እዘምራለሁ
ምኞቴን ሁልጊዜ ትሰጠኝ ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 60: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ