የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 60

60
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በበ​ገ​ና​ዎች የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አም​ላኬ ሆይ፥ ልመ​ና​ዬን ስማኝ፥
ጸሎ​ቴ​ንም አድ​ም​ጠኝ።
2ልቤ ተስፋ በቈ​ረጠ ጊዜ ከም​ድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤
በድ​ን​ጋይ ላይ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።
3በጠ​ላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤
ተስ​ፋ​ዬም ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና መራ​ኸኝ።
4በድ​ን​ኳ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለሁ፤
በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላም እጋ​ረ​ዳ​ለሁ፤
5አም​ላኬ፥ አንተ ጸሎ​ቴን#ዕብ. “ስእ​ለ​ቴን” ይላል። ሰም​ተ​ሃ​ልና፤
ለሚ​ፈ​ሩ​ህም ርስ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው።
6ለን​ጉሥ ከቀን በላይ ቀንን ትጨ​ም​ራ​ለህ፥#በግ​እዝ 3ኛ መደብ።
ዓመ​ታ​ቱም ከት​ው​ልድ ወደ ትው​ልድ ይሆ​ናሉ።
7በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤
ይቅ​ር​ታ​ው​ንና ጽድ​ቁን ማን ይፈ​ል​ጋል?
8እን​ዲሁ ለስ​ምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ
ምኞ​ቴን ሁል​ጊዜ ትሰ​ጠኝ ዘንድ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ