ኀያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኰራለህ? ሁልጊዜስ ለምን ትበድላለህ? ልብህ ኀጢአትን ያስባል፤ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ። ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ። የሚያሰጥም የምላስ ነገርን ሁሉ ወደድህ። ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር። ጻድቃን አይተው ይፍሩ፤ በእርሱም ይሳቁ እንዲህም ይበሉ፦ “እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥ በባለጠግነቱም ብዛት የታመነ፥ በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እነሆ።”
መዝሙረ ዳዊት 51 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 51:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች