መዝሙረ ዳዊት 45
45
ለመዘምራን አለቃ ስለ ምሥጢር የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤
ባገኘን በታላቅ መከራም ጊዜ ረዳታችን ነው።
2ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥
ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈልሱ አንፈራም።
3ውኆቻቸው ጮኹ ደፈረሱም፥
ተራሮችም ከኀይሉ የተነሣ ተናወጡ።
4ፈሳሽ ወንዝ የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛል፤#ዕብ. “የወንዝ ፈሳሾች” ይላል።
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።
5እንዳትታወክም እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው፥
እግዚአብሔርም ፊት ለፊት ይረዳታል።
6አሕዛብ ደነገጡ ነገሥታትም ተመለሱ፤
ልዑል ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።
7የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
8የእግዚአብሔርን ሥራ፥
በምድር ያደረገውንም ተአምራት እንድታዩ ኑ።
9ከምድር ዳርቻ ጦርነትን ይሽራል፤
ቀስትን ይሰብራል፥ ጋሻንም ይቀጠቅጣል፥
በእሳትም የጦር መሣሪያን ያቃጥላል።
10ልብ አድርጉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤
በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥
በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።
11የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 45: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ