የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 45

45
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ስለ ምሥ​ጢር የቆሬ ልጆች መዝ​ሙር።
1አም​ላ​ካ​ችን መጠ​ጊ​ያ​ች​ንና ኀይ​ላ​ችን ነው፤
ባገ​ኘን በታ​ላቅ መከ​ራም ጊዜ ረዳ​ታ​ችን ነው።
2ስለ​ዚህ ምድር ብት​ነ​ዋ​ወጥ፥
ተራ​ሮ​ችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈ​ልሱ አን​ፈ​ራም።
3ውኆ​ቻ​ቸው ጮኹ ደፈ​ረ​ሱም፥
ተራ​ሮ​ችም ከኀ​ይሉ የተ​ነሣ ተና​ወጡ።
4ፈሳሽ ወንዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከተማ ደስ ያሰ​ኛል፤#ዕብ. “የወ​ንዝ ፈሳ​ሾች” ይላል።
ልዑል ማደ​ሪ​ያ​ውን ቀደሰ።
5እን​ዳ​ት​ታ​ወ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ልዋ ነው፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔርም ፊት ለፊት ይረ​ዳ​ታል።
6አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ ነገ​ሥ​ታ​ትም ተመ​ለሱ፤
ልዑል ቃሉን ሰጠ፥ ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች።
7የሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤
የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ መጠ​ጊ​ያ​ችን ነው።
8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥
በም​ድር ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት እን​ድ​ታዩ ኑ።
9ከም​ድር ዳርቻ ጦር​ነ​ትን ይሽ​ራል፤
ቀስ​ትን ይሰ​ብ​ራል፥ ጋሻ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፥
በእ​ሳ​ትም የጦር መሣ​ሪ​ያን ያቃ​ጥ​ላል።
10ልብ አድ​ርጉ፥ እኔም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤
በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ፥
በም​ድ​ርም ላይ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።
11የሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤
የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ መጠ​ጊ​ያ​ችን ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ