የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 44:1-8

መዝ​ሙረ ዳዊት 44:1-8 አማ2000

ልቤ መል​ካም ነገ​ርን ተና​ገረ፥ እኔም ሥራ​ዬን ለን​ጉሥ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አን​ደ​በቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው። ውበቱ ከሰው ልጆች ይልቅ ያም​ራል፤ ሞገስ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ችህ ፈሰሰ፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባረ​ከህ። ኀያል ሆይ፥ በደም ግባ​ት​ህና በው​በ​ትህ፥ ሰይ​ፍ​ህን በወ​ገ​ብህ ታጠቅ። ስለ ቅን​ነ​ትና ስለ የዋ​ህ​ነት ስለ ጽድ​ቅም አቅና፥ ተከ​ና​ወን፥ ንገ​ሥም፤ ቀኝ​ህም በክ​ብር ይመ​ራ​ሃል። ኀያል ሆይ፥ ፍላ​ጻ​ዎ​ችህ የተ​ሳሉ ናቸው፥ አሕ​ዛብ በበ​ታ​ችህ ይወ​ድ​ቃሉ። በን​ጉሥ ጠላ​ቶች ልብ ውስጥ ይገ​ባሉ፥ አም​ላክ ሆይ፥ ዙፋ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ በትረ መን​ግ​ሥ​ትህ የጽ​ድቅ በትር ነው። ጽድ​ቅን ወደ​ድህ፥ ዐመ​ፃ​ንም ጠላህ፤ ስለ​ዚህ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ችህ ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ የደ​ስታ ዘይ​ትን ቀባህ። ከር​ቤና ሽቱ ዝባ​ድም በል​ብ​ሶ​ችህ ናቸው።