የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 43

43
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የቆሬ ልጆች ትም​ህ​ርት።
1አቤቱ፥ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰማን፥
አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዘ​መ​ና​ቸው በቀ​ድሞ ዘመን የሠ​ራ​ኸ​ውን ሥራ ነገ​ሩን።
2እጅህ ጠላ​ትን#ዕብ. “አሕ​ዛብ” ይላል። አጠ​ፋች፥ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ልህ፤
አሕ​ዛ​ብን አሠ​ቃ​የ​ኻ​ቸው፥ አሳ​ደ​ድ​ኻ​ቸ​ውም።
3በጦ​ራ​ቸው ምድ​ርን አል​ወ​ረ​ሱም፥
ክን​ዳ​ቸ​ውም አላ​ዳ​ና​ቸ​ውም፤
ቀኝ​ህና ክን​ድህ የፊ​ት​ህም ብር​ሃን ነው እንጂ፤
ይቅር ብለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና።
4አም​ላ​ኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤
ለያ​ዕ​ቆብ መድ​ኀ​ኒ​ትን ያዘ​ዝህ።
5በአ​ንተ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፥
በስ​ም​ህም በላ​ያ​ችን የቆ​ሙ​ትን እና​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለን።
6በቀ​ስቴ የም​ታ​መን አይ​ደ​ለ​ሁም፥
ጦሬም አያ​ድ​ነ​ኝም፤
7አንተ ግን ከከ​በ​ቡን#ዕብ. “ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን” ይላል። አዳ​ን​ኸን፥
የሚ​ጠ​ሉ​ን​ንም ሁሉ አሳ​ፈ​ር​ሃ​ቸው።
8ሁል​ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ከ​ብ​ራ​ለን፥
ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን።
9አሁን ግን ጣል​ኸን፥ አሳ​ፈ​ር​ኸ​ንም፥#በግ​እዝ ብቻ።
አም​ላ​ካ​ችን፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።
10በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ዘንድ ወደ ኋላ​ችን መለ​ስ​ኸን፥
ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም ተነ​ጣ​ጠ​ቁን።
11እንደ በጎች ሊበ​ሉን ሰጠ​ኸን፥
ወደ አሕ​ዛ​ብም በተ​ን​ኸን፥
12ሕዝ​ብ​ህን ያለ ዋጋ ሰጠህ፥
ለእ​ል​ል​ታ​ች​ንም ብዛት የለ​ውም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመ​ለ​ወ​ጣ​ቸ​ውም ትርፍ የለም” ይላል።
13ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን ስድብ፥
በዙ​ሪ​ያ​ች​ንም ላሉ መሣ​ቂ​ያና መዘ​በቻ አደ​ረ​ግ​ኸን።
14ለአ​ሕ​ዛብ ተረት፥
ለሕ​ዝ​ቡም የራስ መነ​ቅ​ነ​ቂያ አደ​ረ​ግ​ኸን።
15እፍ​ረቴ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው፥
እፍ​ረት ፊቴን ሸፈ​ነኝ።
16ከሚ​ሳ​ደ​ብና ከሚ​ላ​ገድ ቃል የተ​ነሣ፥
ከሚ​ከ​ብብ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚ​ያ​ሳ​ድድ” ይላል። ጠላት ፊት የተ​ነሣ ነው።
17ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥
አል​ረ​ሳ​ን​ህም፥ ኪዳ​ን​ህ​ንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ንም።
18ልባ​ች​ንም ወደ ኋላው አል​ተ​መ​ለ​ሰም፥
ፍለ​ጋ​ች​ንም ከመ​ን​ገ​ድህ ፈቀቅ አላ​ለም፤
19 # ዕብ. “በአ​ራ​ዊት ስፍራ ሰብ​ረ​ኸ​ናል” ይላል። በክፉ ስፍራ አዋ​ር​ደ​ኸ​ና​ልና፥
የሞት ጥላም ሰው​ሮ​ና​ልና፥
20የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ስም ረስ​ተ​ንስ ቢሆን፥
እጃ​ች​ን​ንም ወደ ሌላ አም​ላክ አን​ሥ​ተ​ንስ ቢሆን፥
21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን በተ​መ​ራ​መ​ረው ነበር!
እርሱ ልባ​ችን የሰ​ወ​ረ​ውን ያው​ቃ​ልና።
22ስለ እርሱ#ዕብ. “ስለ አንተ” ይላል። ሁል​ጊዜ ይገ​ድ​ሉ​ና​ልና፥
እን​ደ​ሚ​ታ​ረ​ዱም በጎች ሆነ​ናል።
23አቤቱ፥ ንቃ፤ ለም​ንስ ትተ​ኛ​ለህ?
ተነሥ፥ ለዘ​ወ​ት​ርም አት​ጣ​ለን።
24ለም​ንስ ፊት​ህን ከእኛ ትመ​ል​ሳ​ለህ?
መከ​ራ​ች​ን​ንና ችግ​ራ​ች​ን​ንስ ለምን ትረ​ሳ​ለህ?
25ነፍ​ሳ​ችን በመ​ሬት ላይ ተጐ​ሳ​ቍ​ላ​ለ​ችና፥
ሆዳ​ች​ንም ወደ ምድር ተጣ​ብ​ቃ​ለ​ችና።
26አቤቱ፥ ተነ​ሥና ርዳን፥
ስለ ስም​ህም ተቤ​ዥን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ