በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ፤ እነሆ፥ ከንፈሮችን አልከለክልም፤ አቤቱ፥ አንተ ጽድቄን ታውቃለህ። ቅንነትህን በልቤ ውስጥ አልሰወርሁም፥ ማዳንህንም ተናገርሁ፤ ይቅርታህንና ምሕረትህን ከታላቅ ጉባኤ አልሰወርሁም። አቤቱ አንተ ይቅርታህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ያግኙኝ። ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና፤ ኀጢአቶቼ ተገናኙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ። አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ተመልከት።
መዝሙረ ዳዊት 39 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 39:9-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos