የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 35

35
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ኀጢ​አ​ተኛ ራሱን የሚ​ያ​ስ​ት​በ​ትን ነገር ይና​ገ​ራል፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍር​ሀት በዐ​ይ​ኖቹ ፊት የለም።
2በአ​ን​ደ​በቱ ሸን​ግ​ሎ​አ​ልና፤
ኀጢ​አቱ ባገ​ኘ​ችው ጊዜ ይጠ​ላ​ታል።
3የአፉ ቃል ዐመ​ፅና ሽን​ገላ ነው፤
በጎ ሥራን ይሠራ ዘንድ ማስ​ተ​ዋ​ልን አል​ወ​ደ​ደም።
4በመ​ኝ​ታው ዐመ​ፅን ዐሰበ፤
በሁሉ ነገር መል​ካም ባል​ሆ​ነች መን​ገድ ቆሞ​አል፤
ክፋ​ት​ንም አይ​ሰ​ለ​ቻ​ትም።
5አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ነው፥
እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ትደ​ር​ሳ​ለች።
6ጽድ​ቅ​ህም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራ​ሮች ናት፤
ፍር​ድ​ህም እጅግ ጥልቅ ናት።
7አቤቱ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን ታድ​ና​ለህ።
አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን እንደ አበ​ዛህ፥
የሰው ልጆች በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ ይታ​መ​ናሉ።
8ከቤ​ትህ ጠል ይረ​ካሉ።
ከደ​ስ​ታ​ህም ፈሳሽ ታጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።
9የሕ​ይ​ወት ምንጭ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፤
በብ​ር​ሃ​ንህ ብር​ሃ​ንን እና​ያ​ለን።
10ምሕ​ረ​ት​ህን በሚ​ያ​ው​ቁህ ላይ፥
ጽድ​ቅ​ህ​ንም በልበ ቅኖች ላይ ዘርጋ።
11የት​ዕ​ቢት እግር አይ​ም​ጣ​ብኝ፥
የኀ​ጢ​አ​ተኛ እጅም አያ​ው​ከኝ።
12ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ በዚያ ይወ​ድ​ቃሉ፤
ይሰ​ደ​ዳሉ፥ መቆ​ምም አይ​ች​ሉም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ