የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 33

33
ባሳ​ደ​ደው በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ፊት መል​ኩን በለ​ወጠ ጊዜ፥ በሄ​ደም ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሁል​ጊዜ አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ።
ምስ​ጋ​ና​ውም ዘወ​ትር በአፌ ነው።
2ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትከ​ብ​ራ​ለች፥
ገሮ​ችም ይስሙ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው።
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ አድ​ር​ጉት፥
በአ​ን​ድ​ነ​ትም ስሙን ከፍ ከፍ እና​ድ​ርግ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለ​ግ​ሁት መለ​ሰ​ል​ኝም፥
ከመ​ከ​ራ​ዬም ሁሉ አዳ​ነኝ።
5ወደ እርሱ ቅረቡ ያበ​ራ​ላ​ች​ሁ​ማል፥
ፊታ​ች​ሁም አያ​ፍ​ርም።
6ይህ ችግ​ረኛ ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፥
ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው።
7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በሚ​ፈ​ሩት ሰዎች ዙሪያ
ይሰ​ፍ​ራል፥ ያድ​ና​ቸ​ው​ማል።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወ​ቁም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እዩ” ይላል።
በእ​ርሱ የሚ​ታ​መን ሰው ብፁዕ ነው።
9ለሚ​ፈ​ሩት ችግር የለ​ባ​ቸ​ው​ምና
ቅዱ​ሳን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት።
10ባለ​ጠ​ጎች ደኸዩ፥ ተራ​ቡም፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ል​ጉት ግን ከመ​ል​ካም ነገር ሁሉ አል​ተ​ቸ​ገ​ሩም።
11ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ፤
12ሕይ​ወ​ትን የሚ​ፈ​ቅድ ሰው ማን ነው?
በጎ ዘመ​ን​ንም ለማ​የት የሚ​ወ​ድድ ማን ነው?
13አን​ደ​በ​ት​ህን ከክፉ ከል​ክል፥
ከን​ፈ​ሮ​ች​ህም ሽን​ገ​ላን እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ።
14ከክፉ ሽሽ፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፤
ሰላ​ምን ሻት፥ ተከ​ተ​ላ​ትም።
15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ወደ ጻድ​ቃኑ፥
ጆሮ​ቹም ወደ ልመ​ና​ቸው ናቸ​ውና።
16መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን ከም​ድር ያጠፋ ዘንድ
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉን በሚ​ያ​ደ​ርጉ ላይ ነው።
17ጻድ​ቃን ጮኹ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ​ቸው፥
ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ አዳ​ና​ቸው።
18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በል​ባ​ቸው የዋ​ሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥
በመ​ን​ፈስ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።
19የጻ​ድ​ቃን መከ​ራ​ቸው ብዙ ነው፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሁሉ ያድ​ና​ቸ​ዋል።
20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ይጠ​ብ​ቃል፥
ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ አይ​ሰ​በ​ርም።
21የኃ​ጥእ ሞቱ ክፉ ነው
ጽድ​ቅ​ንም#ዕብ. “ጻድ​ቃ​ንን” ይላል። የሚ​ጠሉ ይጸ​ጸ​ታሉ።
22የባ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ነፍስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቤ​ዣል፥
በእ​ር​ሱም የሚ​ያ​ምኑ ሁሉ አይ​ጸ​ጸ​ቱም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ