መዝሙረ ዳዊት 15
15
የዳዊት ቅኔ።
1አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።
2እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤
በጎነቴን አትሻትምና።#ዕብ. “ያለ አንተ በጎ ነገር የለኝም” ይላል።
3ፈቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳን#ዕብ. “ክቡራን” የሚል ይጨምራል። ላይ ተገለጠ።
4ደዌያቸው በዛ፤ ከዚያም በኋላ ተፋጠኑ፤#ዕብ. “ወደ ሌላ ለሚፋጠኑ መከራቸው ይበዛል” ይላል።
በደም ማኅበራቸው አልተባበርም።
ስማቸውንም በአፌ አልጠራም።
5እግዚአብሔር የርስቴ ዕድል ፋንታና ጽዋዬ ነው፥
ርስቴን የምትመልስ አንተ ነህ።
6ይይዙኝ ዘንድ ገመድ ጣሉብኝ፥
ርስቴ ግን ተያዘልኝ።”#መዝ. 15 ቍ. 6 ዕብ. “ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ ርስቴም ተዋበችልኝ” ይላል።
7እንዳስተውል ያደረገኝን#ዕብ. “የመከረኝን” ይላል። እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤
ደግሞም በሌሊት ኵላሊቶች ይገሥጹኛል።
8ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤
እንዳልታወክ በቀኜ ነውና።
9ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ምላሴም ሐሤት አደረገ፤
ሥጋዬ ደግሞ በተስፋው ያድራል፤
10ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥
ጻድቅህንም#ዕብ. “ቅዱስህን” ይላል። መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።
11የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤
ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥
በቀኝህም የዘለዓለም ፍስሓ አለ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 15: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ