መዝሙረ ዳዊት 119
119
የመዓርግ መዝሙር።
1አቤቱ፥ በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማኸኝም።
2ከዐመፀኛ ከንፈር፥ ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
3ስለ ሽንገላ አንደበት ምንን ይሰጡሃል?
ምንስ ይጨምሩልሃል?
4እንደ በረሃ ቋያ የኀያል ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።
5መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፤
በዘላን ድንኳኖች አደርሁ።
6ሰላምን ከሚጠሉ ጋር
ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገሠች።
7እኔ ሰላማዊ ስሆን
በተናገርኋቸው ጊዜ በከንቱ ይጠሉኛል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 119: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ