የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 118:1-14

መዝ​ሙረ ዳዊት 118:1-14 አማ2000

በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ንጹ​ሓን የሆኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው። ምስ​ክ​ሩን የሚ​ፈ​ልጉ፥ በፍ​ጹም ልብ የሚ​ሹት ብፁ​ዓን ናቸው፤ ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን በመ​ን​ገዱ አይ​ሄ​ዱም። ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን እጅግ ይጠ​ብቁ ዘንድ አንተ አዘ​ዝህ። ሥር​ዐ​ት​ህን እጠ​ብቅ ዘንድ የሚ​ቀ​ናስ ከሆነ መን​ገዴ ይቅና። ትእ​ዛ​ዝ​ህን ሁሉ ስመ​ለ​ከት በዚ​ያን ጊዜ አላ​ፍ​ርም። አቤቱ፥ የጽ​ድ​ቅ​ህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ። ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ጣ​ለኝ። ጐል​ማሳ መን​ገ​ዱን በምን ያቀ​ናል? ቃል​ህን በመ​ጠ​በቅ ነው። በፍ​ጹም ልቤ ፈለ​ግ​ሁህ፥ ከት​እ​ዛ​ዝህ አታ​ር​ቀኝ። አን​ተን እን​ዳ​ል​በ​ድል፥ ቃል​ህን በልቤ ሰወ​ርሁ። አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ። የአ​ፍ​ህን ፍርድ ሁሉ በከ​ን​ፈሬ ነገ​ርሁ። እንደ ብል​ጥ​ግና ሁሉ በም​ስ​ክ​ርህ መን​ገድ ደስ አለኝ።