መጽሐፈ ምሳሌ 4:10-19

መጽሐፈ ምሳሌ 4:10-19 አማ2000

ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤ የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል፥ የሕይወትህ መንገድ ይበዛ ዘንድ። የጥበብን መንገዶች አስተምርሃለሁና፤ በቀናች ጎዳና መራሁህ። ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤ በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም። ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና። በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትቅና። በተጓዙበትም ቦታ አትሂድ፤ ከእነርሱ ፈቀቅ በል ተመለስም። ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም። የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥ በግፍ የወይን ጠጅም ይሰክራሉ። የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ። ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ። የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው። እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።