ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ የምነግርህንም ስማ፤ ዕድሜህም ይረዝማል። የጥበብን መንገድ አሳየሁህ፤ በቀና መንገድም መራሁህ። በጥበብ ብትራመድ እርምጃህ አይታገድም፤ ብትሮጥም አትሰናከልም። የተማርከው ትምህርት ሕይወትን ስለሚሰጥህ አጥብቀህ ያዘው፤ አትተወው፤ ደኅና አድርገህም ጠብቀው። ክፉ ሰዎች በሚሄዱበት መንገድ አትሂድ፤ ምሳሌነታቸውንም አትከተል። ከእርሱ ራቅ፤ በዚያም አትራመድ፤ ከእርሱ ርቀህ በራስህ መንገድ ሂድ። ክፉ ነገር ካላደረጉ ዕረፍት አይኖራቸውም፤ በሰው ላይ ጒዳት ካላደረሱ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ። ዐመፅና ግፍ ለእነርሱ እንደ መብልና እንደ መጠጥ ናቸው። የደጋግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ የቀኑ ሙሉ ብርሃን እስኪሆን ድረስ ብርሃኑ እየጨመረ ይሄዳል። የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ይወድቃሉ፤ የመውደቂያቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ አያውቁም።
መጽሐፈ ምሳሌ 4 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ምሳሌ 4:10-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos