አንተን ከክፉ መንገድ፥ ምንም የሚታመን ነገርን ከማይናገር ሰውም ታድንህ ዘንድ፥ እነርሱ በጨለማ መንገድ ይሄዱ ዘንድ የቀናውን ጎዳና ለሚተዉ፥ ክፉ በመሥራት ደስ ለሚላቸው ክፋትንም በመመለስ ሐሤትን ለሚያደርጉ፥ መንገዳቸው ጐጻጕጽ፥ አካሄዳቸው ጠማማ ለሆኑ ወዮላቸው! ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤ ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከሌላዪቱ ክፉ ሴት፥ የሕፃንንነት ባልዋን ከምትተው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከምትረሳ፤ ይጠብቅህ ዘንድ፤ ቤቷን በሞት አጠገብ አኖረች፥ አካሄድዋንም ከኀያላን ጋር ከምድር ወደ ሲኦል አቀናች። ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ቀና መንገዶችንም አያገኙም፥ ሕይወት በአለው ዘመንም አይገኙም። ቀና መንገዶችን ቢሄዱ ለስላሳ የጽድቅ መንገዶችን ባገኙ ነበር።
መጽሐፈ ምሳሌ 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ምሳሌ 2:12-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች