ጥበብ ከክፉ ሰዎች መንገድና ከጠማማ ንግግራቸው ያድንሃል። እንደነዚህ ዐይነት ሰዎች በኃጢአት ጨለማ ውስጥ ለመኖር የጽድቅን መንገድ የተዉ ናቸው። እነርሱን ደስ የሚያሰኛቸው ቀናውን ነገር ማጣመምና ተንኰል የተሞላበት ክፉ ሥራ መሥራት ነው። እነርሱ እምነት የማይጣልባቸውና ጠማሞች ናቸው። እንግዲህ እኔ የምልህን ብትሰማ በልዝብ አነጋገር ከምታጠምድ ከአመንዝራ ሴት ማምለጥ ትችላለህ። እንደዚህ ያለችው ሴት ለልጅነት ባልዋ ያላትን ታማኝነት የምታጓድልና በእግዚአብሔር ፊት የገባችውንም ቃል ኪዳን የምትዘነጋ ናት። ወደ እርስዋ ቤት ብታመራ ጒዞህ ወደ ሞት ይሆናል፤ ወደ እርስዋ መሄድ ወደ ሙታን ዓለም እንደ መውረድ ነው። ወደ እርስዋ የሚሄድ ሁሉ አይመለስም፤ የሕይወትንም ጐዳና ማግኘት አይችልም። ስለዚህ የመልካም ሰዎችን ምሳሌነት ልትከተልና የደጋግ ሰዎችንም አካሄድ ልትጠብቅ ይገባሃል።
መጽሐፈ ምሳሌ 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ምሳሌ 2:12-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች