የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 19

19
1በከንፈሩ ከሚወሳልት አላዋቂ ይልቅ፥
ያለ ነውር የሚሄድ ድሃ ይሻላል።
2ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤
እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።#ምዕ. 19 ቁ. 1 እና 2 በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በግእዝ የሉም።
3የሰው ስንፍናው መንገዱን ያጣምምበታል፥
በልቡም እግዚአብሔርን ገፋኢ ያደርገዋል።
4ባለጠጋ ብዙ ወዳጆችን ይጨምራል፤
ድሃ ግን ያን ያለውን ያጣል።
5ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥
በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።
6ብዙ ሰዎች በነገሥታት ፊት ያገለግላሉ፥
ነገር ግን የሰው ጽድቁና ሀብቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤#“ነገር ግን የሰው ጽድቁና ሀብቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ክፉ ሁሉም የሰው መዘባበቻ ይሆናል።
7ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥
ከወንድምነቱ የራቀ ነው።
በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች።
ብልህ ሰውም ያገኛታል።
ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥
ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም።
8ጥበብን የሚያገኝ ራሱን ይወድዳል፥
ማስተዋልንም የሚጠብቅ መልካም ነገርን ያገኛል።
9ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤
ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል።
10ለአላዋቂ ቅምጥልነት አይገባውም፥
አገልጋይም ከስድብ ጋር ቢገዛ ይበረታል።
11ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥
መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥
12የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥
ሞገሱም በመስክ ላይ እንዳለ ጠል ነው።
13አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ኀፍረት ነው፥
ከዐስበ ደነስ ጋር የሚቀርብ ስእለትም ንጹሕ አይደለም።
14አባቶች ለልጆቻቸው ቤትንና ሀብትን ያወርሳሉ፤
ሚስት ግን በእግዚአብሔር ከባልዋ ጋር አንድ ትሆናለች።
15ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥
የማይሠራ ሰውም ይራባል።
16ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤
መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል።
17ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥
እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።
18ለተስፋ ይሆንህ ዘንድ ልጅህን ግረፍ፥
ለመሳደብ ግን እጅህን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰውነትህን ...” ይላል። አታንሣ፥
19ዐሳበ ክፉ ሰው ብዙ ያጠፋል፤
ጽኑ ደፋር ቢሆን ግን ነፍሱን ይጨምራል።
20ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥
በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።
21በሰው ልብ ብዙ ዐሳብ አለ፤
የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል።
22ምጽዋት ለሰው ፍሬ ነው፤
ከሐሰተኛ ባለጠጋም እውነተኛ ድሃ ይሻላል።
23እግዚአብሔርን መፍራት የሰው ሕይወት ነው፤
የማይፈራው ግን ዕውቀት በሌለበት ቦታ ውስጥ ይኖራል።
24ታካች ሰው እጁን በብብቱ ይሸሽጋል፥
ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።
25ፌዘኛን ብትገርፈው አላዋቂው ብልሃተኛ ይሆናል፤
አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው ግን ዕውቀትን ያገኛል።
26አባቱን የሚያዋርድ እናቱንም የሚያሳድድ፥
አሳፋሪና ጐስቋላ ልጅ ይሆናል።
27የአባቱን ትምህርት ከመጠበቅ የሚከለከል ልጅ፥
ክፉ ቃልን ይማራል።
28ለአላዋቂ ልጅ የሚዋስ ፍርድን ያስነቅፋል፥
የኃጥኣንም አፍ ክፉ ቅጣትን ይውጣል።
29ለክፉዎች ሰዎች መቅሠፍት ተዘጋጅቶላቸዋል፥
ለሰነፎችም እንደዚሁ ቅጣት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ