የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 1:12-30

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 1:12-30 አማ2000

ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ይህ የደ​ረ​ሰ​ብኝ በእ​ው​ነት ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ፋ​ፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ። ስለ ክር​ስ​ቶስ ስም መታ​ሰ​ሬም በአ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉና በሰው ሁሉ ዘንድ ታው​ቆ​አል። ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ብዙ​ዎቹ በእ​ስ​ራቴ ምክ​ን​ያት በጌታ ታመኑ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያለ ፍር​ሀት ጨክ​ነው ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ እጅግ ተደ​ፋ​ፈሩ። ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶች በቅ​ና​ታ​ቸ​ውና በክ​ር​ክ​ራ​ቸው፥ ሌሎ​ችም በበጎ ፈቃድ ስለ ክር​ስ​ቶስ ሊሰ​ብ​ኩና ሊያ​ስ​ተ​ምሩ የወ​ደዱ አሉ። በፍ​ቅር የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩም አሉ፤ ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር እንደ ተሾ​ምሁ ያው​ቃ​ሉና። በኵ​ራት ስለ ክር​ስ​ቶስ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ግን፥ ይህን አድ​ር​ገው በእ​ስ​ራቴ ላይ መከራ ሊጨ​ም​ሩ​ብኝ መስ​ሎ​አ​ቸው ነው እንጂ በእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ን​ነ​ትም አይ​ደ​ለም። ነገር ግን ምን አለ? በየ​ም​ክ​ን​ያቱ በእ​ው​ነ​ትም ቢሆን፥ በሐ​ሰ​ትም ቢሆን፥ ስለ ክር​ስ​ቶስ ይና​ገ​ራሉ፤ ሰው​ንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠ​ራሉ፤ በዚ​ህም ደስ ብሎ​ኛል፤ ወደ​ፊ​ትም ደስ ይለ​ኛል። እኔም ይህቺ ሥራ በጸ​ሎ​ታ​ች​ሁና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ወደ ሕይ​ወት እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ሰኝ አው​ቃ​ለሁ። በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል። እኔ በሕ​ይ​ወት ብኖ​ርም ክር​ስ​ቶ​ስን ለማ​ገ​ል​ገል ነው፤ ብሞ​ትም ዋጋ አለኝ። ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም። በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከ​ክ​ር​ስ​ቶ​ስም ዘንድ ልኖር እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ለእኔ ይህ ይሻ​ለ​ኛል፤ ይበ​ል​ጥ​ብ​ኛ​ልም። ደግ​ሞም ስለ እና​ንተ በሕ​ይ​ወተ ሥጋ ብኖር ይሻ​ላል። ይህ​ንም ዐውቄ ለማ​ደ​ጋ​ች​ሁና በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ለም​ታ​ገ​ኙት ደስታ እን​ደ​ም​ኖር አም​ና​ለሁ። ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ። ነገር ግን ምና​ል​ባት የመ​ጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳል​ኖ​ርም ቢሆን በወ​ን​ጌል ሃይ​ማ​ኖት እየ​ተ​ጋ​ደ​ላ​ችሁ በአ​ንድ መን​ፈ​ስና በአ​ንድ አካል ጸን​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራ​ችሁ ለክ​ር​ስ​ቶስ ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ገባ ይሁን። የእ​ነ​ርሱ ጥፋት፥ የእ​ና​ን​ተም ሕይ​ወት ይታ​ወቅ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙን ሰዎች በማ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ደ​ን​ግ​ጧ​ችሁ። ይህ​ንም ጸጋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልት​ቀ​በ​ሉም ነው እንጂ ልታ​ም​ኑ​በት ብቻ አይ​ደ​ለም። እን​ዲ​ሁም እኔን እን​ዳ​ያ​ች​ሁኝ፥ የእ​ኔ​ንም ነገር እንደ ሰማ​ችሁ ምን​ጊ​ዜም ተጋ​ደሉ።