የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 2

2
የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ በሰ​ፈር አመ​ዳ​ደብ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦ 2“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ በየ​ሥ​ር​ዐቱ፥ በየ​ዓ​ላ​ማው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ አን​ጻር ይስ​ፈሩ። 3በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ። 4የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ሰባ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። 5በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የይ​ሳ​ኮር ነገድ ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች አለቃ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል ነበረ። 6የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 7በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የዛ​ብ​ሎን ነገድ ነበረ፤ የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች አለቃ የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ ነበረ። 8የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 9ከይ​ሁዳ ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ ሰማ​ንያ ስድ​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ይጓ​ዛሉ።
10“በአ​ዜብ በኩል በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የሮ​ቤል ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የሮ​ቤ​ልም ልጆች አለቃ የሴ​ድ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር ነበረ። 11የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ ስድ​ስት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። 12በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የስ​ም​ዖን ነገድ ናቸው፤ የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች አለቃ የሲ​ሩ​ሳዴ ልጅ ሰላ​ም​ያል ነበረ። 13የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። 14በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የጋድ ነገድ ነበረ፤ የጋ​ድም ልጆች አለቃ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤል​ሳፍ ነበረ። 15የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ አምሳ ነበሩ። 16ከሮ​ቤል ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ነበሩ። እነ​ር​ሱም ቀጥ​ለው ይጓ​ዛሉ።
17“ከዚ​ያም በኋላ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ በሰ​ፈ​ሮ​ቹም መካ​ከል የሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ይጓ​ዛል፤ እንደ አሰ​ፋ​ፈ​ራ​ቸው ሰው ሁሉ በየ​ስ​ፍ​ራው፥ በየ​ዓ​ላ​ማ​ውም ይጓ​ዛሉ።
18“በባ​ሕር በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የኤ​ፍ​ሬም ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለቃ የኤ​ሜ​ሁድ ልጅ ኤሌ​ሳማ ነበረ። 19የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። 20በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የም​ናሴ ነገድ ይሆ​ናል፤ የም​ና​ሴም ልጆች አለቃ የፈ​ዳ​ሱር ልጅ ገማ​ል​ያል ነበረ። 21የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 22በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የብ​ን​ያም ነገድ ይሆ​ናል፤ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች አለቃ የጋ​ዴ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን ነበረ። 23የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም፥ ሠላሳ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 24ከኤ​ፍ​ሬም ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ ስም​ንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሦስ​ተኛ ሆነው ይጓ​ዛሉ።
25“በመ​ስዕ በኩል እንደ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆ​ናል፤ የዳ​ንም ልጆች አለቃ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አክ​ያ​ዜር ነበረ። 26የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። 27በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የአ​ሴር ነገድ ይሆ​ናሉ፤ የአ​ሴ​ርም ልጆች አለቃ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋጋ​ኤል ነበረ። 28የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አርባ አንድ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። 29በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የን​ፍ​ታ​ሌም ነገድ ይሆ​ናል፤ የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች አለቃ የዔ​ናን ልጅ አኪሬ ነበረ። 30የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 31ከዳን ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። እነ​ር​ሱም በየ​ዓ​ላ​ማ​ቸው በመ​ጨ​ረሻ ይጓ​ዛሉ።”
32ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ እነ​ዚህ ናቸው፤ ከየ​ሰ​ፈሩ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ። 33ሌዋ​ው​ያን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም። 34የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ እን​ዲሁ በየ​ዓ​ላ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ሰፈሩ፤ እን​ዲ​ሁም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ተጓዙ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ