የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 12

12
አሮ​ንና ማር​ያም ሙሴን እንደ ተቃ​ወ​ሙት
1ሙሴም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ቱን ሴት አግ​ብ​ቶ​አ​ልና ባገ​ባት በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊቱ ሴት ምክ​ን​ያት ማር​ያ​ምና አሮን አሙት። 2እነ​ር​ሱም፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ብቻ ተና​ግ​ሮ​አ​ልን? በእ​ኛስ ደግሞ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ። 3ሙሴም በም​ድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የዋህ ሰው ነበረ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወዲ​ያው ሙሴ​ንና አሮ​ንን ማር​ያ​ም​ንም፥ “ሦስ​ታ​ችሁ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ኑ ብሎ ተና​ገረ፤ ሦስ​ቱም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ወጡ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መና ዐምድ ወረደ፤ በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ ቆመ፤ አሮ​ን​ንና ማር​ያ​ም​ንም ጠራ​ቸው፤ ሁለ​ቱም ወጡ። 6እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ። 7አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታ​መነ ነው። 8እኔ አፍ ለአፍ በግ​ልጥ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በስ​ው​ርም አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ያያል፤ አገ​ል​ጋዬ ሙሴን ማማ​ትን ስለ ምን አል​ፈ​ራ​ች​ሁም?” አለ።
9የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ በእ​ነ​ርሱ ላይ ወረደ፤ እር​ሱም ሄደ። 10ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ ተነሣ፤ እነ​ሆም፥ ማር​ያም ለም​ጻም ሆነች፤ እንደ በረ​ዶም ነጭ ሆነች፤ አሮ​ንም ማር​ያ​ምን ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ለም​ጻም ሆና ነበር። 11አሮ​ንም ሙሴን፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ስን​ፍና አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በድ​ለ​ን​ማ​ልና እባ​ክህ፥ ኀጢ​አት አታ​ድ​ር​ግ​ብን። 12ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ሞቶ እንደ ተወ​ለደ፥ ከተ​በላ ግማሽ ሥጋዋ ጋር ለሞት አት​ተ​ዋት።” 13ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እየ​ጮኸ፥ “አቤቱ፥ እባ​ክህ፥ አድ​ናት” አለው። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራ​ቁን በፊቷ ቢተ​ፋ​ባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገ​ባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰ​ፈር ውጭ ተዘ​ግታ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመ​ለስ” አለው። 15ማር​ያ​ምም ከሰ​ፈር ውጭ ሰባት ቀን ተለ​ይታ ተቀ​መ​ጠች፤ ማር​ያ​ምም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ሕዝቡ አል​ተ​ጓ​ዙም።
16ከዚ​ያም በኋላ ሕዝቡ ከአ​ሴ​ሮት ተጓዙ፤ በፋ​ራ​ንም ምድረ በዳ ሰፈሩ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 12 በቍ. 15 ያበ​ቃል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ