የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 8:27-33

የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 8:27-33 አማ2000

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሣርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ፤ በመንገድም “ሰዎች እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ?” ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው። እነርሱም “መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ” ብለው ነገሩት። “እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ ነህ፤” ብሎ መለሰለት። ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው። የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊናቅ፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር። ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር። እርሱ ግን ዘወር አለ፤ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውና “ወደ ኋላዬ ሂድ! አንተ ሰይጣን! የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና፤” አለ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች