የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 12:1-12

የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 12:1-12 አማ2000

በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። በጊዜውም ከወይን አትክልት ፍሬ ከገበሬዎቹ እንዲቀበል አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤ ይዘውም ደበደቡት፤ ባዶውንም ሰደዱት። ዳግመኛም ሌላውን ባሪያ ወደ እነርሱ ላከ፤ እርሱንም ወግረው ራሱን አቈሰሉት፤ አዋርደውም ሰደዱት። ሌላውንም ላከ፤ እርሱንም ገደሉት፤ ከሌሎችም ከብዙዎች አንዳንዱን ደበደቡ፤ አንዳንዱንም ገደሉ። የሚወደው አንድ ልጅ ገና ነበረው፤ ‘ልጄንስ ያፍሩታል፤’ ብሎ እርሱን ከሁሉ በኋላ ወደ እነርሱ ላከ። እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለው፤ ርስቱም ለኛ ይሆናል፤’ ተባባሉ። ይዘውም ገደሉት፤ ከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ ጣሉት። እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል? ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ያጠፋል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል። ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?” ምሳሌውንም ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አውቀዋልና ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። ትተውትም ሄዱ።