ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን በምሳሌ እንዲህ ሲል ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ዙሪያውንም ዐጠረ፤ የወይን መጭመቂያ የሚሆን ጒድጓድ ቆፍሮ አበጀ፤ ለወይኑ ጥበቃ የሚያገለግል ከፍተኛ የግንብ ማማ ሠራ፤ ከዚህም በኋላ የአትክልቱን ቦታ ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። ፍሬው በደረሰ ጊዜ፥ ከወይኑ ፍሬ እንዲያመጣለት አገልጋዩን ወደ ገበሬዎቹ ላከ። ገበሬዎቹ ግን አገልጋዩን ይዘው ከደበደቡት በኋላ ባዶ እጁን ሰደዱት። እንደገና ባለቤቱ ሌላ አገልጋይ ላከ፤ ገበሬዎቹ ይህንንም በድንጋይ ፈንክተውና አዋርደው ሰደዱት። ቀጥሎም ሌላውን ቢልክ ገደሉት፤ እንዲሁም ብዙዎችን ቢልክ፥ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ ሌሎቹንም ገደሉ። አሁን ማድረግ የቀረው የሚወደውን ልጁን መላክ ብቻ ነበር፤ ስለዚህ ‘ልጄንስ ያከብሩት ይሆናል’ ብሎ በማሰብ በመጨረሻ አንድ ልጁን ላከ። ነገር ግን ገበሬዎቹ እርስ በርሳቸው ‘ይህማ ወራሹ ነው! ኑ እንግደለው! ርስቱም ለእኛ ይሆናል’ ተባባሉ። ስለዚህ ልጁን ይዘው ገደሉት፤ ከወይኑ ተክልም ቦታ ውጪ ጣሉት። “እንግዲህ የወይኑ ተክል ጌታ ምን ያደርጋል? ባለቤቱ ራሱ ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ይገድላል፤ የወይኑንም ተክል ለሌሎች ይሰጣል። ለመሆኑ፥ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነ፤ ይህም የጌታ ሥራ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ ” የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል አላነበባችሁምን? የአይሁድ አለቆች ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ እነርሱን የሚመለከት መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈርተው ትተውት ሄዱ።
የማርቆስ ወንጌል 12 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማርቆስ ወንጌል 12:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች