ሕዝቡም ዐውቀው ተከተሉት፤ እርሱም ተቀበላቸው፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም አስተማራቸው፤ ሊፈወሱ የሚሹትንም አዳናቸው። ቀኑም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፥ “ያለንበት ምድረ በዳ ነውና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩ የሚበሉትንም እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት” አሉት። እርሱ ግን፥ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው” አላቸው፤ እነርሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ልንገዛ ካልሄድን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለንም” አሉት። ሰዎቹም አምስት ሺህ ያህሉ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱንም፥ “አምሳ አምሳውን በየክፍላቸው አስቀምጡአቸው” አላቸው። እንዲሁም አደረጉ፤ ሁሉም ተቀመጡ። አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመለከተ፤ ባረከ፤ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ያነሡትም የተረፈው ቍርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።
የሉቃስ ወንጌል 9 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 9
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 9:11-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች