ከዚህም በኋላ በሌላይቱ ሰንበት ወደ ምኵራቡ ገባና አስተማራቸው፤ በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ። ጻፎችና ፈሪሳውያንም የሚከሱበት ምክንያት ያገኙ ዘንድ፥ በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ብለው ይጠባበቁት ነበር። እርሱ ግን ዐሳባቸውን ያውቅባቸው ነበርና እጁ የሰለለችውን ሰው፥ “ተነሥተህ በመካከል ቁም” አለው፤ ተነሥቶም ቆመ። ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እጠይቃችኋለሁ፤ በሰንበት ሊደረግ የሚገባው ምንድነው? መልካም መሥራት ነውን? ወይስ ክፉ መሥራት? ነፍስን ማዳን ነውን? ወይስ መግደል?” እነርሱም ዝም አሉ፤ ወደ እነርሱም ዙሮ ከተመለከተ በኋላ፦ ያን ሰው፥ “እጅህን ዘርጋ” አለው፤ ሰውዬውም ዘረጋት፤ እጁም ዳነችና እንደ ሁለተኛይቱ ሆነች። እነርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌታችን በኢየሱስም ምን እንድሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተማከሩ። በዚያም ወራት ጌታችን ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፤ ሲነጋም ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠራቸው፤ ከውስጣቸውም ዐሥራ ሁለቱን መረጠ፤ ሐዋርያት ብሎም ሰየማቸው። እነርሱም እነዚህ ናቸው፦ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን፥ ወንድሙም እንድርያስ፥ ያዕቆብና ዮሐንስ፥ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ። ማቴዎስና ቶማስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ቀናዒ የሚባለው ስምዖን። የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፥ የከዳውና አሳልፎ የሰጠው ያስቆሮቱ ሰው ይሁዳም ናቸው።
የሉቃስ ወንጌል 6 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 6
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 6:6-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች