የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 24:33-49

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 24:33-49 አማ2000

በዚ​ያ​ችም ሰዓት ተነ​ሥ​ተው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ዐሥራ አን​ዱን ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ት​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው አገ​ኙ​አ​ቸው፤ እን​ዲህ እያሉ፥ “ጌታ​ችን በእ​ው​ነት ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ለስ​ም​ዖ​ንም ታይ​ቶ​ታል።” እነ​ር​ሱም በመ​ን​ገድ የሆ​ነ​ው​ንና እን​ጀ​ራ​ውን ሲቈ​ርስ ጌታ​ች​ንን እን​ዴት እን​ዳ​ወ​ቁት ነገ​ሩ​አ​ቸው። ይህ​ንም ሲነ​ጋ​ገሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አት​ፍሩ፤ እኔ ነኝ” አላ​ቸው። እነ​ርሱ ግን ፈሩ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ ምት​ሐ​ት​ንም የሚ​ያዩ መሰ​ላ​ቸው። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ኋል? በል​ባ​ች​ሁስ እን​ዲህ ያለ ዐሳብ ለምን ይነ​ሣ​ሣል? እጄ​ንና እግ​ሬን እዩ፤ ዳስ​ሱ​ኝም፤ እኔ እንደ ሆን​ሁም ዕወቁ፤ በእኔ እን​ደ​ም​ታ​ዩት ለም​ት​ሐት አጥ​ን​ትና ሥጋ የለ​ው​ምና።” ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና እግ​ሮ​ቹን አሳ​ያ​ቸው። ከድ​ን​ጋጤ የተ​ነ​ሣም ገና ሳያ​ምኑ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ሲያ​ደ​ንቁ ሳሉ፥ “በዚህ አን​ዳች የሚ​በላ አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ከተ​ጠ​በሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፤ ከማር ወለ​ላም ጥቂት ሰጡት። ተቀ​ብ​ሎም በፊ​ታ​ቸው በላ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም አን​ሥቶ ሰጣ​ቸው። እር​ሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነ​ቢ​ያ​ትና በመ​ዝ​ሙ​ርም ስለ እኔ የተ​ነ​ገ​ረው ይፈ​ጸም ዘንድ እን​ዳ​ለው፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላ​ቸው። ከዚ​ህም በኋላ መጻ​ሕ​ፍ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ተ​ውሉ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ከፈ​ተ​ላ​ቸው። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥ ንስ​ሓና የኀ​ጢ​ኣት ስር​የት ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጀምሮ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ሰ​በክ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አል። እና​ን​ተም ለዚህ ነገር ምስ​ክ​ሮች ናችሁ። እነሆ፥ እኔ የአ​ባ​ቴን ተስፋ ለእ​ና​ንተ እል​ካ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ከአ​ር​ያም ኀይ​ልን እስ​ክ​ት​ለ​ብሱ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከተማ ተቀ​መጡ።”

Free Reading Plans and Devotionals related to የሉ​ቃስ ወን​ጌል 24:33-49