የሉ​ቃስ ወን​ጌል 23:33-37

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 23:33-37 አማ2000

ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባ​ለው ቦታ በደ​ረሱ ጊዜም፥ በዚያ ሰቀ​ሉት፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎች አን​ዱን በቀኙ አን​ዱ​ንም በግ​ራው ሰቀሉ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ። ሕዝ​ቡም ቆመው ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ አለ​ቆ​ችም፥ “ሌሎ​ችን አዳነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ክር​ስ​ቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌ​ዙ​በት ነበር። ጭፍ​ሮ​ችም ይዘ​ብ​ቱ​በት ነበር፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው ሆም​ጣጤ አመ​ጡ​ለት። እን​ዲ​ህም ይሉት ነበር፥ “አንተ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ከሆ​ን​ህስ ራስ​ህን አድን።”