የሉ​ቃስ ወን​ጌል 23:26-29

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 23:26-29 አማ2000

በወ​ሰ​ዱ​ትም ጊዜ የቀ​ሬና ሰው ስም​ዖ​ንን ከዱር ሲመ​ለስ ያዙት፤ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱ​ስም በስ​ተ​ኋላ መስ​ቀ​ሉን አሸ​ከ​ሙት። ብዙ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ሴቶ​ችም “ዋይ ዋይ” እያሉ ያዝ​ኑ​ለ​ትና ያለ​ቅ​ሱ​ለት ነበሩ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጆች ሆይ፥ ለራ​ሳ​ች​ሁና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አል​ቅሱ እንጂ ለእ​ኔስ አታ​ል​ቅ​ሱ​ልኝ። መካ​ኖች፥ ያል​ወ​ለዱ ማኅ​ፀ​ኖ​ችና ያላ​ጠቡ ጡቶ​ችም የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው የሚ​ሉ​በት ወራት ይመ​ጣ​ልና።