በዚያ ሀገር እረኞች ነበሩ፤ ሌሊቱንም ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ነበር። እነሆም፥ የእግዚአብሔር መልአክ በአጠገባቸው ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው አበራ፤ ታላቅ ፍርሀትንም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው፥ “እነሆ፥ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ። እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው። ለእናንተም ምልክቱ እንዲህ ነው፦ ሕፃን አውራ ጣቱን ታስሮ፥ በጨርቅም ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኛላቸሁ።” ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ። “ክብር ለእግዚአብሔር በሰማያት፥ ሰላምም በምድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር። ከዚህም በኋላ መላእክት ከእነርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በዐረጉ ጊዜ እነዚያ እረኞች ሰዎች እርስ በርሳቸው፥ “እስከ ቤተ ልሔም እንሂድ፤ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን ነገር እንወቅ” አሉ። ፈጥነውም ሄዱ፤ ማርያምንና ዮሴፍን አገኙአቸው፤ ሕፃኑንም በበረት ውስጥ ተኝቶ አገኙት። በአዩም ጊዜ የነገሩአቸው ስለዚህ ሕፃን እንደ ሆነ ዐውቀው አወሩ።
የሉቃስ ወንጌል 2 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 2
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 2:8-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos