የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 16:19-26

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 16:19-26 አማ2000

“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር። በቍ​ስል ሕመም ተይዞ በባ​ለ​ጸ​ጋው ደጅ የወ​ደቀ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል አንድ ድሃም ነበረ። ከባ​ለ​ጸ​ጋው ማዕድ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ው​ንም ፍር​ፋሪ ሊመ​ገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾ​ችም እየ​መጡ ቍስ​ሉን ይል​ሱት ነበር። ከዚ​ህም በኋላ ድሃው ሞተ፤ መላ​እ​ክ​ትም ወደ አብ​ር​ሃም አጠ​ገብ ወሰ​ዱት፤ ባለ​ጸ​ጋ​ውም ደግሞ ሞተ፤ ተቀ​በ​ረም፤ በሲ​ኦ​ልም በሥ​ቃይ ሳለ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ አብ​ር​ሃ​ምን ከሩቅ አየው፤ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጦ አየው። ‘አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ እዘ​ን​ልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠ​ቃ​ይ​ቻ​ለ​ሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላ​ሴን ያቀ​ዘ​ቅ​ዝ​ልኝ ዘንድ አል​ዓ​ዛ​ርን ላከው’ ብሎ ተጣራ። አብ​ር​ሃም ግን እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕ​ይ​ወ​ትህ ተድ​ላና ደስታ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ በች​ጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እን​ዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድ​ላና ደስታ ያደ​ር​ጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀ​በ​ላ​ለህ። ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እና​ንተ ማለፍ የሚሹ እን​ዳ​ይ​ችሉ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የሆ​ኑ​ትም ወደ እኛ እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ታላቅ ገደል አለ’