የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 14:17-20

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 14:17-20 አማ2000

ለምሳ የተ​ጠ​ሩ​በ​ትም ቀን በደ​ረሰ ጊዜ የታ​ደ​ሙ​ትን ይጠ​ራ​ቸው ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱም ሄዶ የታ​ደ​ሙ​ትን፦ አሁን ምሳ​ውን ፈጽ​መን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ና​ልና ኑ አላ​ቸው። ሁሉም በአ​ንድ ቃል ተባ​ብ​ረው እንቢ አሉ፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው፦ እርሻ ገዝ​ች​አ​ለሁ፤ ሄጄም ላያት እሻ​ለሁ፤ እንቢ እንደ አላ​ልሁ ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው። ሁለ​ተ​ኛ​ውም፦ አም​ስት ጥማድ በሬ ገዝ​ቻ​ለሁ፤ ላያ​ቸ​ውና ልፈ​ት​ና​ቸው እሄ​ዳ​ለሁ፤ እንደ መጣሁ፥ እንቢ እንደ አላ​ል​ሁም ቍጠ​ር​ልኝ በለው አለው። ሦስ​ተ​ኛ​ውም፦ ሚስት አግ​ብ​ች​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ልመጣ አል​ች​ልም በለው አለው።