ሉቃስ 14:17-20
ሉቃስ 14:17-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የግብዣውም ሰዓት በደረሰ ጊዜ የተጋበዙትን እንግዶች፣ ‘እነሆ፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቷልና ኑ’ ብሎ እንዲጠራ ባሪያውን ላከባቸው። “ነገር ግን ሁሉም የየራሳቸውን ምክንያት ይፈጥሩ ጀመር፤ አንደኛው፣ ‘ገና አሁን መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ እባክህ፣ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው። “ሌላውም፣ ‘ዐምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ፤ እነርሱን ልፈትናቸው ስለ ሆነ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ። “ሌላው ደግሞ፣ ‘ገና ሙሽራ ስለ ሆንሁ ልመጣ አልችልም’ አለ።
ሉቃስ 14:17-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለምሳ የተጠሩበትም ቀን በደረሰ ጊዜ የታደሙትን ይጠራቸው ዘንድ አገልጋዩን ላከ፤ እርሱም ሄዶ የታደሙትን፦ አሁን ምሳውን ፈጽመን አዘጋጅተናልና ኑ አላቸው። ሁሉም በአንድ ቃል ተባብረው እንቢ አሉ፤ የመጀመሪያው፦ እርሻ ገዝችአለሁ፤ ሄጄም ላያት እሻለሁ፤ እንቢ እንደ አላልሁ ቍጠርልኝ በለው አለው። ሁለተኛውም፦ አምስት ጥማድ በሬ ገዝቻለሁ፤ ላያቸውና ልፈትናቸው እሄዳለሁ፤ እንደ መጣሁ፥ እንቢ እንደ አላልሁም ቍጠርልኝ በለው አለው። ሦስተኛውም፦ ሚስት አግብችአለሁ፤ ስለዚህ ልመጣ አልችልም በለው አለው።
ሉቃስ 14:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በእራትም ሰዓት የታደሙትን፦ አሁን ተዘጋጅቶአልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ። ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የፊተኛው፦ መሬት ገዝቼአለሁ ወጥቼም ላየው በግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው። ሌላውም፦ አምስት ጥምድ በሬዎች ገዝቼአለሁ ልፈትናቸውም እሄዳለሁ፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው። ሌላውም፦ ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው።
ሉቃስ 14:17-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የግብዣው ሰዓት በደረሰ ጊዜ፥ ‘እነሆ፥ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶአልና ወደ ግብዣው ኑ!’ ብሎ እንዲነግራቸው ጋባዡ አገልጋዩን ወደ ተጠሩት ሰዎች ላከው። ነገር ግን እያንዳንዱ ተጋባዥ ከግብዣው ለመቅረት ምክንያት መስጠት ጀመረ፤ አንዱ ‘መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ ስለዚህ መምጣት አልችልምና ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው። ሌላው ‘አምስት ጥንድ በሬዎች ስለ ገዛሁ እነርሱን መፈተን አለብኝ፤ ስለዚህ መምጣት አልችልምና ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ። ሌላው ደግሞ ‘ሚስት አግብቼ ሙሽራ ስለ ሆንኩ ልመጣ አልችልም’ አለ።
ሉቃስ 14:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በእራትም ሰዓት የታደሙትን ‘አሁን ሁሉ ተዘጋጅቶአልና ኑ’ እንዲላቸው አገልጋዩን ላከ። ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የመጀመሪያው ‘መሬት ገዝቼአለሁ፤ ወጥቼም ላየው የግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ፤’ አለው። ሌላውም ‘አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቼአለሁ፤ ለመፈተንም እሄዳለሁ፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ፤’ አለው። ሌላውም ‘ሚስት አግብቼአለሁ፤ ስለዚህም ልመጣ አልችልም’ አለው።