ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 6

6
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦ 2“ሰው ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትእ​ዛዝ ቸል ቢል፥ ያኖ​ረ​በ​ትን አደራ ወይም የኅ​ብ​ረ​ትን ገን​ዘብ ወስዶ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ግፍ ቢሠራ፥ 3ወይም የጠ​ፋ​ውን ነገር ቢያ​ገኝ፥ ስለ​ዚ​ህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢ​አ​ትን ለመ​ሥ​ራት ከሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ በአ​ን​ዲቱ በሐ​ሰት ቢምል፥ 4እርሱ ቢበ​ድ​ልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅ​ድ​ሚያ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወይም በዐ​መ​ፅና በግፍ የተ​ቀ​በ​ለ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​ጠ​ውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገ​ኘ​ውን፥ 5ወይም በሐ​ሰት የማ​ለ​በ​ትን ነገር ቢመ​ልስ፥ በሙሉ ይመ​ልስ፤ ከዚ​ያም በላይ አም​ስ​ተ​ኛ​ውን ክፍል ጨምሮ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ቀ​ር​ብ​በት ቀን#ግእዙ “በዕ​ለተ ዘለ​ፍዎ” ይላል። ለባለ ገን​ዘቡ ይስ​ጠው። 6ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕ​ትም ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ።#ዕብ. “ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ በግ እንደ ግም​ጋ​ሜህ መጠን ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ወደ ካህኑ ያምጣ” ይላል።7ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ስለ​ዚ​ያም ስለ አደ​ረ​ገው በደል ሁሉ ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።”
ስለ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሕግ
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 9“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ የሚ​ቃ​ጠ​ለው የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ሕግ ይህ ነው፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው እሳት በላዩ እየ​ነ​ደ​ደች እስ​ኪ​ነጋ ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ። 10ካህ​ኑም የተ​ልባ እግር ቀሚ​ስና የተ​ልባ እግር ሱሪ በሰ​ው​ነቱ ላይ ይለ​ብ​ሳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት እሳቱ ከበ​ላው በኋላ አመ​ዱን አን​ሥቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል። 11ልብ​ሱ​ንም ያወ​ል​ቃል፤ ሌላም ልብስ ይለ​ብ​ሳል፤ አመ​ዱ​ንም ተሸ​ክሞ ከሰ​ፈሩ ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ወደ ውጭ ያወ​ጣ​ዋል። 12እሳ​ቱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ዘወ​ትር ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም፤ ካህ​ኑም ማለዳ ማለዳ ዕን​ጨት ያቃ​ጥ​ል​በ​ታል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በዚያ ላይ ይረ​በ​ር​ባል፤ በዚ​ያም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ስብ ያቃ​ጥ​ላል። 13ዘወ​ትር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም።
ስለ እህል ቍር​ባን
14“የአ​ሮን ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ለፊት የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የመ​ሥ​ዋ​ዕት#ዕብ. “የእ​ህል ቍር​ባን” ይላል። ሥር​ዐት ይህ ነው። 15ካህ​ኑም ከእ​ህሉ ቍር​ባን መል​ካ​ሙን የስ​ንዴ ዱቄት ከዘ​ይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግ​ሞም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያለ​ውን ዕጣን ሁሉ ያነ​ሣል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ ያለው የመ​ታ​ሰ​ቢያ ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ነውና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። 16ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን አሮ​ንና ልጆቹ ይበ​ሉ​ታል፤ ቂጣ ሆኖ በተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይበ​ላል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ባለው አደ​ባ​ባይ ይበ​ሉ​ታል። 17በእ​ርሾ ቦክቶ አይ​ጋ​ገ​ርም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሰ​ጠ​ኋ​ቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እር​ሱም እንደ ኀጢ​አ​ትና እንደ በደል መሥ​ዋ​ዕት ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። 18ከካ​ህ​ናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በዘ​መ​ና​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ነው። ከሚ​ቃ​ጠ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።”
19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦ 20“እር​ሱን በቀ​ባ​ህ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ መባ ይህ ነው። የኢፍ መስ​ፈ​ርያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካ​ሙን ዱቄት እኩ​ሌ​ታ​ውን በጥ​ዋት፥ እኩ​ሌ​ታ​ው​ንም በማታ ለዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባሉ። 21ከዘ​ይት ጋር በም​ጣድ ላይ ያደ​ር​ጉ​ታል፤ ለው​ሰ​ውም ያገ​ቡ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ፈ​ተት መሥ​ዋ​ዕት ነው። 22ከል​ጆ​ቹም በእ​ርሱ ፋንታ የተ​ቀ​ባው ካህን ያቀ​ር​በ​ዋል። ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው፤ ሁል​ጊ​ዜም ይደ​ረ​ጋል። 23ካህ​ና​ትም የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች አይ​በ​ላም።”
ስለ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረያ መሥ​ዋ​ዕት
24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦ 25“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታ​ረ​ዳል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። 26የሚ​ሠ​ዋው ካህን ይበ​ላ​ዋል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ በአ​ለው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይበ​ሉ​ታል። 27ሥጋ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ ማና​ቸ​ውም ልብስ ደም ቢረ​ጭ​በት የተ​ረ​ጨ​በ​ትን በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ያጥ​ቡ​ታል። 28የሚ​ቀ​ቀ​ል​በ​ትን ሸክላ ይሰ​ብ​ሩ​ታል፤ በና​ስም ዕቃ ቢቀ​ቀል ይፈ​ገ​ፍ​ጉ​ታል፤ በው​ኃም ያጥ​ቡ​ታል። 29ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእ​ርሱ ይበ​ላል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። 30ነገር ግን በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ገ​ባው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ አይ​በ​ላም፤ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 6 ከቍ. 31 እስከ 40 ያለው በዕብ. እና በግ​እዝ ምዕ. 7 ከቍ. 1 እስከ 10 ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ