የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢዩ​ኤል 1

1
የአ​ን​በጣ መንጋ መዓት
1ወደ ባቱ​ኤል ልጅ ወደ ኢዮ​ኤል የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው። 2እና​ንተ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች! ይህን ስሙ፤ በም​ድ​ርም የም​ት​ኖሩ ሁሉ አድ​ምጡ። ይህ በዘ​መ​ና​ችሁ ወይስ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ዘመን ሆኖ ነበ​ርን? 3ይህን ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ንገሩ፤ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ለል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ለኋ​ለ​ኛው ትው​ልድ ይን​ገሩ። 4ከተ​ምች የቀ​ረ​ውን አን​በጣ በላው፤ ከአ​ን​በ​ጣም የቀ​ረ​ውን ደጎ​ብያ በላው፤ ከደ​ጎ​ብ​ያም የቀ​ረ​ውን ኩብ​ኩባ በላው።
5እና​ንተ ሰካ​ራ​ሞች፥ ንቁ፤ ለመ​ስ​ከ​ርም ወይ​ንን የም​ት​ጠጡ እና​ንተ ሁላ​ችሁ! ተድ​ላና ደስታ ከአ​ፋ​ችሁ ጠፍ​ት​ዋ​ልና አል​ቅሱ፤ እዘ​ኑም። 6ቍጥ​ርም የሌ​ለው ብርቱ ሕዝብ በም​ድሬ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ጥር​ሳ​ቸው እንደ አን​በሳ ጥርስ፥ ክን​ዳ​ቸ​ውም እንደ አን​በሳ ደቦል ክንድ ነው። 7ወይ​ኔን ባዶ ምድር አደ​ረ​ገው፤ በለ​ሴ​ንም ሰበ​ረው፤ ተመ​ለ​ከ​ተ​ውም፥ ጣለ​ውም፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ነጡ።
8ስለ ልጅ​ነት ባልዋ ማቅ ለብሳ እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅስ ድን​ግል አል​ቅሺ። 9መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተወ​ግ​ዶ​አል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሠ​ውያ የም​ታ​ገ​ለ​ግሉ ካህ​ናቱ፥ አል​ቅሱ። 10እር​ሻው ምድረ በዳ ሆኖ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም ታል​ቅስ፤ እህሉ ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ ወይ​ኑም ደር​ቆ​አ​ልና፥ ዘይ​ቱም ጐድ​ሎ​አ​ልና። 11መከሩ ከእ​ር​ሻ​ቸው ጠፍ​ቶ​አ​ልና ገበ​ሬ​ዎች ስለ ስን​ዴ​ውና ስለ ገብሱ ዐፈሩ፤ የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞ​ችም ስለ ወይኑ አለ​ቀሱ። 12ወይኑ ደር​ቆ​አል፤ በለ​ሱም ጠፍ​ቶ​አል፤ ሮማ​ኑና ተምሩ፥ እን​ኮ​ዩም፥ የም​ድ​ርም ዛፎች ሁሉ ደር​ቀ​ዋል፤ ደስ​ታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆ​አል።
13መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት ቀር​ቶ​አ​ልና እና​ንተ ካህ​ናት! ማቅ ታጥ​ቃ​ችሁ አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የመ​ሠ​ውያ አገ​ል​ጋ​ዮች! ዋይ በሉ፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ። 14ጾምን ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንና በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሰብ​ስቡ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ጩኹ።
15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና ለቀኑ ወዮ! ወዮ! እር​ሱም በጥ​ፋት ላይ እንደ ጥፋት ይመ​ጣል። 16ከዐ​ይ​ኖ​ቻ​ችሁ ፊት ምግብ፥ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ቤት ደስ​ታና ሐሤት ጠፍ​ቶ​አል። 17ጊደ​ሮች#ዕብ. “ዘሩ በም​ድር ውስጥ በሰ​በሰ” ይላል። ከም​ሳ​ጋ​ቸው ጠፉ፤ ጎተ​ራ​ዎች ባዶ ሆኑ፤ ዐው​ድ​ማ​ዎ​ቹም ፈራ​ረሱ፤ እህሉ ደር​ቆ​አ​ልና። 18እን​ግ​ዲህ ለራ​ሳ​ችን ምን እን​ሰ​ብ​ስብ? የእ​ን​ስ​ሳት ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቀሱ፤ ማሰ​ማ​ሪያ የላ​ቸ​ው​ምና፥ የበ​ጎች መን​ጋ​ዎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋ​ልና። 19አቤቱ! እሳት የም​ድረ በዳ​ውን ውበት አጥ​ፍ​ቶ​አ​ልና፥ ነበ​ል​ባ​ሉም የዱ​ሩን ዛፍ ሁሉ አቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ። 20ፈሳሹ ውኃ ደር​ቆ​አ​ልና፥ እሳ​ቱም የም​ድረ በዳ​ውን ውበት በል​ቶ​አ​ልና የም​ድር አራ​ዊት ወደ አንተ አን​ጋ​ጠጡ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}