እግዚአብሔርም እንደገና በደመና ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰለት፥ እንዲህም አለ፦ “እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም መልስልኝ። ወይም ፍርዴን መቃወምህን ተው፥ ጽድቅህ እንድትገለጥ እንጂ እኔ በሌላ መንገድ የምፈርድብህ ይመስልሃልን? እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጕዳለህን? እስኪ ልዕልናንና ኀይልን ተላበስ፤ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። የቍጣህን መላእክት ላክ፤ ትዕቢተኛውንም ሁሉ አዋርደው። ትዕቢተኛውን ሰው ዝቅ ዝቅ አድርገው፤ ዝንጉዎችንም በአንድ ጊዜ አጥፋቸው። በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፤ ፊታቸውንም በኀፍረት ሙላ። በዚያን ጊዜ ቀኝ እጅህ ታድንህ ዘንድ እንድትችል፥ እኔ ደግሞ እመሰክርልሃለሁ። “እነሆ፥ በአንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል። እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፤ ኀይሉም በሆዱ እንብርት ውስጥ ነው። ጅራቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወዛውዛል፤ የወርቹም ጅማት የተጐነጐነ ነው። የጐድን አጥንቱ እንደ ናስ ነው፤ የጀርባው አጥንቶችም እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው። ይህ የእግዚአብሔር የፍጥረቱ አውራ ነው። ከተፈጠረም በኋላ መላእክት ሣቁበት። ወደ ረዥም ተራራ በወጣ ጊዜም በሜዳው ላሉ እንስሳት በጥልቁ ስፍራ ደስታን ያደርጋል። ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደንገል፥ በቄጠማና በሸንበቆ ሥር ይተኛል። ጥላ ያለው ዛፍ በጥላው ይሰውረዋል፤ የወንዝ አኻያ ዛፎችም ይከብቡታል። እነሆ፥ ወንዙ ቢጐርፍ አይደነግጥም፤ ዮርዳኖስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈስስ እርሱ ይተማመናል። ዐይኑ እያየ በገመድ ይያዛልን? አፍንጫውስ ይበሳልን?
መጽሐፈ ኢዮብ 40 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢዮብ 40:6-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች