የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 37

37
1“ስለ​ዚ​ህም ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ች​ብኝ፥
ከስ​ፍ​ራ​ዋም ተን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰች።
2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቍ​ጣ​ውን ድምፅ ስማ፥
ከአ​ፉም የሚ​ወ​ጣ​ውን ጕር​ም​ር​ምታ አድ​ምጥ።
3እር​ሱን ወደ ሰማ​ያት ሁሉ ታች፥
ብር​ሃ​ኑ​ንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰ​ድ​ዳል።
4በስ​ተ​ኋ​ላው ድምፅ ይጮ​ኻል፤
በግ​ር​ማ​ውም ድምፅ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤
ድም​ፁም በተ​ሰማ ጊዜ ሰዎች እን​ዲ​ጠፉ አያ​ደ​ር​ግም።
5ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ምፁ ድንቅ አድ​ርጎ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤
ለእ​ን​ስ​ሳት በየ​ጊ​ዜው ምግ​ባ​ቸ​ውን ያዘ​ጋ​ጃል፥ የሚ​ተ​ኙ​በ​ት​ንም ጊዜ ያው​ቃሉ፤
በዚህ ሁሉ ልብህ አይ​ደ​ን​ግ​ጥ​ብህ፤
ሥጋ​ህም ልብ​ህም ከግ​ዘፉ አይ​ለ​ወ​ጥ​ብህ፤
እር​ሱም እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን ታላቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።#ምዕ. 37 ቍ. 5 ላይ 2ኛ፥ 3ኛ እና 4ኛ መስ​መ​ሮች በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 36 ቍ. 28 ይገ​ኛል።
6በረ​ዶ​ው​ንና ውሽ​ን​ፍ​ሩን፥ ብር​ቱ​ው​ንም ዝናብ
በም​ድር ላይ እን​ዲ​ወ​ርድ ያዝ​ዛል።
7ሰው ሁሉ ደካ​ማ​ነ​ቱን ያውቅ ዘንድ፥
የሰ​ውን ሁሉ እጅ ያት​ማል።
8አው​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ጫካው ይገ​ባሉ፥
በዋ​ሾ​ቻ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ።
9ከተ​ሰ​ወረ ማደ​ሪ​ያ​ውም ችግር፥
ከተ​ራ​ሮች ጫፍም ብርድ ይመ​ጣል።
10ከኀ​ያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ት​ን​ፋስ ውርጭ ይመ​ጣል።
ውኃ​ው​ንም እንደ ወደደ ይመ​ራ​ዋል።
11የተ​መ​ረ​ጡ​ትን በደ​መና ይሰ​ው​ራል፤#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
ብር​ሃ​ኑም ደመ​ና​ውን ይበ​ት​ናል፤
12እር​ሱም ሰው በሚ​ኖ​ር​በት ዓለም ላይ፥
ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያደ​ርግ ዘንድ፥
ፈቃዱ ወደ መራ​ችው ይዞ​ራል።
13ይኸ​ውም፥ ለተ​ግ​ሣጽ
ወይም ለም​ድሩ ወይም በም​ሕ​ረት ለሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲ​ሆን ነው።
14“ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤
ቁም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይል ተገ​ሠጽ።
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ውን እን​ዳ​ከ​ና​ወነ
ከጨ​ለ​ማም ለይቶ ብር​ሃ​ንን እንደ ፈጠረ እና​ው​ቃ​ለን።#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
16የደ​መ​ና​ትን ክፍ​ሎች፥
አስ​ፈሪ የሆ​ነ​ው​ንም የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን አወ​ዳ​ደቅ ያው​ቃል።
17የአ​ዜብ ነፋስ በተ​ኮሰ ጊዜ ያንተ ልብ​ስህ የሞቀ ነው።
እን​ግ​ዲህ በም​ድር ላይ ፀጥ በል።
18እንደ ቀለጠ መስ​ተ​ዋት
ብርቱ የሆ​ኑ​ትን ሰማ​ያት ከእ​ርሱ ጋር ልት​ዘ​ረጋ ትች​ላ​ለ​ህን?
19ስለ​ዚህ ንገ​ረኝ! ምን እን​ለ​ዋ​ለን?
እን​ግ​ዲህ ዝም እን​በል፥ ብዙም አን​ና​ገር፥
20“ሰው በእኔ ዘንድ ሲቆም ዝም እል ዘንድ፥
መጽ​ሐፍ ወይም ጸሓፊ አለ​ኝን?#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
21“ብር​ሃን ለሁሉ የሚ​ታይ አይ​ደ​ለም
ብር​ሃን በእ​ርሱ ዘንድ በደ​መና ውስጥ ሆኖ
ከሩቅ በሰ​ማ​ያት ያበ​ራል።
22ከሰ​ሜን እንደ ወርቅ የሚ​ያ​በራ ደመና ይወ​ጣል፤
በዚ​ህም ሁሉን የሚ​ችል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ክብ​ርና ምስ​ጋና አለ።
23በኀ​ይል ከእ​ርሱ ጋር እኩል የሚ​ሆን፥#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
እው​ነ​ት​ንም የሚ​ፈ​ርድ ሌላ አና​ገ​ኝም።
እርሱ እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ታስ​ባ​ለ​ህን?
24ስለ​ዚህ ሰዎች ይፈ​ሩ​ታል፤
በል​ባ​ቸ​ውም ጠቢ​ባን የሆኑ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ