መጽሐፈ ኢዮብ 35
35
ኢዮብ ራሱን በማጽደቁ ኤልዩስ እንደ ተቃወመ
1ኤልዩስም ደግሞ መለሰ፥ እንዲህም አለ፦
2“አንተ ተዋቅሰህ ምን ትላለህ?
ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ የምትል አንተ ማን ነህ?
3ኀጢአት ብሠራስ ምን አደርጋለሁ? ትላለህ።#በዕብ. ልዩ ነው።
4እኔ ለአንተና ለሦስቱ ወዳጆችህ እመልሳለሁ።
5ወደ ሰማይ ተመልከት፥ እይም፤
ደመናም ከአንተ በላይ ምን ያህል ከፍ እንዳለ ዕወቅ።
6ኀጢአት ብትሠራ በእርሱ ላይ ምን ታደርጋለህ?
ብዙም ብትበድል ምን ማድረግ ትችላለህ?
7ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ?
ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል?
8እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጎዳዋል፤
ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።
9ከግፈኞች ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፤
ከብዙዎች ክንድ የተነሣም ለርዳታ ይጠራሉ።
10ነገር ግን በሌሊት ጥበቃን የሚያዝዝ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር
ወዴት ነው? የሚል የለም፤
11እርሱም ከምድር እንስሶች ይልቅ፥
ከሰማይም ወፎች ይልቅ የሚለየኝ ነው።
12በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ስድብ ይጮኻሉ፥
እርሱ ግን አይሰማቸውም።
13እግዚአብሔር በእውነት ክፉ ነገርን ሊያይ አይወድም።
እርሱ ሁሉን የሚችል ዐዋቂ አምላክ ነውና።
14ክፉ የሚሠሩትን አይሰማቸውም፥ እኔንም ያድነኛል፤
አንተ አሁን የሚቻል እንደ መሆኑ መጠን
ልታመሰግነው ትችል እንደ ሆነ እስኪ በፊቱ ተዋቀስ።#በዕብራይስጥ ይለያል።
15አሁን ቍጣውን የሚያውቅ የለምና፥
ታላቅ ኀጢአቱንም የሚያስብ የለምና።
16ኢዮብ ግን አፉን በከንቱ ይከፍታል፥
ያለ ዕውቀትም ቃሉን ያበዛል።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 35: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ