የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 25

25
የበ​ል​ዳ​ዶስ ንግ​ግር
1አው​ኬ​ና​ዊ​ውም በል​ዳ​ዶስ መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“ጥን​ቱን መፈ​ራት በእ​ርሱ ዘንድ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን?
በከ​ፍ​ታ​ውም ሁሉን ነገር አድ​ራጊ ነው።#ዕብ. “... ሰላ​ምን አደ​ረገ” ይላል።
3ለሌ​ቦች ዕረ​ፍ​ትን የሚ​ሰጥ እን​ዳለ የሚ​መ​ስ​ለው አይ​ኑር።#ዕብ. ልዩ​ነት አለው።
የክ​ፋ​ቱስ ወጥ​መድ የማ​ይ​መ​ጣ​በት ማን ነው?
4ጻድቅ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሟች” ይላል። ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ንጹሕ ይሆ​ናል?
ከሴ​ትስ የተ​ወ​ለደ ራሱን ንጹሕ ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?
5እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ይሰ​ወ​ራል፤ አያ​በ​ራ​ምም፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እርሱ ለጨ​ረቃ ትእ​ዛዝ ቢሰጥ አታ​በ​ራም” ይላል።
ከዋ​ክ​ብ​ትም በፊቱ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ሉም።
6ይል​ቁ​ንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥
ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ