መጽሐፈ ኢዮብ 25
25
የበልዳዶስ ንግግር
1አውኬናዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
2“ጥንቱን መፈራት በእርሱ ዘንድ ያለ አይደለምን?
በከፍታውም ሁሉን ነገር አድራጊ ነው።#ዕብ. “... ሰላምን አደረገ” ይላል።
3ለሌቦች ዕረፍትን የሚሰጥ እንዳለ የሚመስለው አይኑር።#ዕብ. ልዩነት አለው።
የክፋቱስ ወጥመድ የማይመጣበት ማን ነው?
4ጻድቅ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሟች” ይላል። ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ንጹሕ ይሆናል?
ከሴትስ የተወለደ ራሱን ንጹሕ ማድረግ እንዴት ይችላል?
5እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ይሰወራል፤ አያበራምም፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እርሱ ለጨረቃ ትእዛዝ ቢሰጥ አታበራም” ይላል።
ከዋክብትም በፊቱ ንጹሓን አይደሉም።
6ይልቁንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥
ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 25: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ