የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 2:11-13

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 2:11-13 አማ2000

ሦስ​ቱም የኢ​ዮብ ወዳ​ጆች ይህን የደ​ረ​ሰ​በ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰም​ተው ከየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነ​ር​ሱም ቴማ​ና​ዊው ንጉሥ ኤል​ፋዝ፥ አው​ኬ​ና​ዊው መስ​ፍን በል​ዳ​ዶስ፥ አሜ​ና​ዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሊጐ​በ​ኙ​ትና ሊያ​ጽ​ና​ኑት በአ​ን​ድ​ነት ወደ እርሱ መጡ። ከሩ​ቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላ​ወ​ቁ​ትም፤ በታ​ላቅ ድም​ፅም ጮኸው አለ​ቀሱ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ። ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​መጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስ​ፈ​ሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ አንድ ቃል የሚ​ና​ገ​ረው አል​ነ​በ​ረም።