የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 12

12
የኢ​ዮብ መልስ
1ኢዮ​ብም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“በእ​ር​ግጥ እና​ንተ ዓይ​ነ​ተ​ኞች ሰዎች ናችሁ፤
ጥበ​ብም በእ​ና​ንተ ዘንድ ትፈ​ጸ​ማ​ለች።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይሞ​ታል” ይላል።
3ነገር ግን እኔ ደግሞ እንደ እና​ንተ ልብ አለኝ።
እኔ ከእ​ና​ንተ የማ​ንስ አይ​ደ​ለ​ሁም፥
እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር የሚ​ያ​ውቅ ማነው?#“እኔ ከእ​ና​ንተ የማ​ንስ አይ​ደ​ለ​ሁም እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጠ​ራሁ እር​ሱም የመ​ለ​ሰ​ልኝ እኔ፥
ለባ​ል​ን​ጀ​ራው መሣ​ለ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ሆን ሰው ሆኛ​ለሁ፤
ጻድ​ቁና ንጹሑ ሰው መሣ​ለ​ቂያ ሆኖ​አል።#የምዕ. 12 ቍ. 4 የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁለት መስ​መ​ሮች በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የሉም።
5እርሱ በተ​ወ​ሰ​ነው ዕድሜ በሌ​ሎች እን​ዲ​ወ​ድቅ፥
ቤቱም በኃ​ጥ​ኣን እን​ዲ​ፈ​ርስ ተዘ​ጋ​ጅቶአል።
ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እን​ደ​ሚ​ሆን አይ​መን።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡ​ትን ሰዎች፥
እርሱ የሚ​መ​ረ​ም​ራ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?
7“አሁን ግን እን​ስ​ሶ​ችን ጠይቅ፥ ያስ​ተ​ም​ሩ​ህ​ማል፤
የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች ጠይቅ፥ ይነ​ግ​ሩ​ህ​ማል።
8ለም​ድር ንገ​ራት፥
እር​ስ​ዋም ትተ​ረ​ጕ​ም​ል​ሃ​ለች፤
የባ​ሕ​ርም ዓሣ​ዎች ያስ​ረ​ዱ​ሃል።
9የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይህን ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረገ
ከእ​ነ​ዚህ ሁሉ የማ​ያ​ውቅ ማን ነው?
10የሕ​ያ​ዋን ሁሉ ነፍስ፥
የሰ​ውም ሁሉ መን​ፈስ በእጁ ናትና።
11ዦሮ ነገ​ርን የሚ​ለይ አይ​ደ​ለ​ምን?
ጕረ​ሮስ#ዕብ. “ምላስ” ይላል። መብ​ልን የሚ​ቀ​ምስ አይ​ደ​ለ​ምን?
12በረ​ዥም ዘመን ጥበብ፥
በመ​ኖር ብዛ​ትም ዕው​ቀት ይገ​ኛል።
13በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ጥበ​ብና ኀይል አለ፤
ለእ​ርሱ ምክ​ርና ማስ​ተ​ዋል አለው።
14እነሆ፥ እርሱ ቢያ​ፈ​ርስ፥ ማን ይሠ​ራል?
በሰ​ውም ላይ ቢዘ​ጋ​በት ማን ይከ​ፍ​ታል?
15እነሆ፥ ዝና​ብን ከሰ​ማይ ቢከ​ለ​ክል ምድ​ርን ያደ​ር​ቃ​ታል፤
እን​ደ​ገና ቢተ​ዋ​ትም ትጠ​ፋ​ለች፤ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለ​ችም።
16ኀይ​ልና ብር​ታት በእ​ርሱ ዘንድ ናቸው፤
ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋ​ልም ለእ​ርሱ ናቸው።
17መካ​ሮ​ች​ንም እን​ዲ​ማ​ረኩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤
የም​ድር ፈራ​ጆ​ች​ንም አላ​ዋ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።
18ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም በዙ​ፋን ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤
ወገ​ባ​ቸ​ው​ንም በኀ​ይል መታ​ጠ​ቂያ ያስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል።
19ካህ​ናተ ጣዖ​ትን እን​ዲ​ማ​ረኩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤
የም​ድር ኀያ​ላ​ን​ንም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል።
20ከታ​መኑ ሰዎ​ችም ቋን​ቋን ይለ​ው​ጣል፤
የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም ምክር ያው​ቃል።
21በአ​ለ​ቆች ላይ ውር​ደ​ትን ያመ​ጣል፥
ትሑ​ታ​ን​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።
22ጥልቅ ነገ​ርን ከጨ​ለማ ይገ​ል​ጣል፤
የሞ​ት​ንም ጥላ ወደ ብር​ሃን ያወ​ጣል።
23አሕ​ዛ​ብን ያቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ልም፤
አሕ​ዛ​ብ​ንም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ልም።
24የም​ድር አለ​ቆች ማስ​ተ​ዋ​ልን ይለ​ው​ጣል።
በማ​ያ​ው​ቁት መን​ገ​ድም ያቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ቸ​ዋል።
25ብር​ሃ​ንም ሳይ​ኖር በጨ​ለማ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ፤
እንደ ሰካ​ራ​ምም ይፍ​ገ​መ​ገ​ማሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ