የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:46-54

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:46-54 አማ2000

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ውኃ​ውን የወ​ይን ጠጅ ወደ አደ​ረ​ገ​በት የገ​ሊላ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ቃና ዳግ​መኛ ሄደ። በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ልጁ የታ​መ​መ​በት የን​ጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከይ​ሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበ​ርና ወርዶ ልጁን ያድ​ን​ለት ዘንድ ለመ​ነው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ምል​ክ​ት​ንና ድንቅ ሥራን ካላ​ያ​ችሁ አታ​ም​ኑም” አለው። ያም የን​ጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይ​ሞት ፈጥ​ነህ ውረድ” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂድ፤ ልጅ​ህስ ድኖ​አል” አለው፤ ያም ሰው፦ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በነ​ገ​ረው ቃል አምኖ ሄደ። ሲወ​ር​ድም አገ​ል​ጋ​ዮቹ ተቀ​በ​ሉ​ትና፥ “ልጅ​ህስ ድኖ​አል” ብለው ነገ​ሩት። የዳ​ነ​ባ​ትን ሰዓ​ቷ​ንም ጠየ​ቃ​ቸው፤ “ትና​ን​ትና በሰ​ባት ሰዓት ንዳዱ ተወው” አሉት። አባ​ቱም፥ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “ልጅህ ድኖ​አል” ባለ​በት ሰዓት እንደ ሆነች ዐወቀ፤ እር​ሱም፥ ቤተ ሰቦ​ቹም ሁሉ አመኑ። ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከይ​ሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደ​ረ​ገው ሁለ​ተ​ኛው ተአ​ምር ይህ ነው።