የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 21:15-22

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 21:15-22 አማ2000

ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፦ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስን፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ከእ​ነ​ዚህ ይልቅ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “በጎ​ችን ጠብቅ” አለው። ዳግ​መ​ኛም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “ጠቦ​ቶ​ችን አሰ​ማራ” አለው። ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው። “እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ አንተ ጐል​ማሳ ሳለህ በገዛ እጅህ ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ወደ ወደ​ድ​ኸው ትሄድ ነበር፤ በሸ​መ​ገ​ልህ ጊዜ ግን እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፤ ወገ​ብ​ህ​ንም ሌላ ያስ​ታ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ወደ​ማ​ት​ወ​ደ​ውም ይወ​ስ​ድ​ሃል።” በምን ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያከ​ብር ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክት ይህን ተና​ገረ፤ ይህ​ንም ብሎ ተከ​ተ​ለኝ አለው። ጴጥ​ሮ​ስም መለስ ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በ​ረ​ውን ያን ደቀ መዝ​ሙር ሲከ​ተ​ለው አየ፤ እር​ሱም ራት ሲበሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውና “ጌታ ሆይ፥ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥህ ማነው?” ያለው ነው። ጴጥ​ሮ​ስም እር​ሱን አይቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ ይህስ እን​ዴት ይሆ​ናል?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እስ​ክ​መጣ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ፤ አንተ ግን ተከ​ተ​ለኝ” አለው።