የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 2:6-11

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 2:6-11 አማ2000

በዚ​ያም እንደ አይ​ሁድ ልማድ የሚ​ያ​ነ​ጹ​ባ​ቸው ስድ​ስት የድ​ን​ጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁለት ወይም ሦስት እን​ስራ ይይዙ ነበር። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ጋኖ​ቹን ውኃ ሙሉ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እስከ አፋ​ቸ​ውም እስከ ላይ ሞሉ​አ​ቸው። “አሁ​ንም ቅዱና ወስ​ዳ​ችሁ ለአ​ሳ​ዳ​ሪው ስጡት” አላ​ቸው፤ ወስ​ደ​ውም ሰጡት። አሳ​ዳ​ሪ​ውም ያን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ውኃ ቀምሶ አደ​ነቀ፤ ከወ​ዴት እንደ መጣም አላ​ወ​ቀም፤ የቀ​ዱት አሳ​ላ​ፊ​ዎች ግን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃ​ዉን የሞሉ እነ​ርሱ ነበ​ሩና። አሳ​ዳ​ሪ​ውም ሙሽ​ራ​ውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ አስ​ቀ​ድሞ ያጠ​ጣል፤ ከጠ​ገቡ በኋ​ላም ተር​ታ​ውን ያመ​ጣል፤ አንተ ግን መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ እስ​ካ​ሁን አቈ​የህ” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።